Read the Beforeitsnews.com story here. Advertise at Before It's News here.
Profile image
By Electronic Frontier Foundation (Reporter)
Contributor profile | More stories
Story Views
Now:
Last hour:
Last 24 hours:
Total:

ባለፈረጀ ብዙውን የኢትዮጵያ መንግሥት የስለላ ተግባር መከላከል፤ እራስን ከስለላ የመከላከያ ብልሃቶች መመሪያ በአማርኛ ተዘጋጅቷል

% of readers think this story is Fact. Add your two cents.


ከቴሌኮሙኒኬሽን እስከ ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ስርጭት ያሉ የሕዝብ መገናኛዎች በኢትዮጵያ መንግሥት ቁጥጥር ሥር ናቸው። ይህም መንግሥት በአጠቃላይ የመገናኛ የልማት አውታሮች ላይ ሙሉ የበላይነቱን መያዙ፤ ግላዊነት እና ሌሎች ግንኙነቶች በግልጽ ለስለላ ምቹ ኾነዋል ማለት ነው። በአንዳንድ አጋጣሚዎች የመንግሥትን የተጠናከረ እና ውስብስብ የስለላ መረብ አልፈው የሚደረጉ ግንኙነቶች ቢኖሩ እንኳ በየመንደሩ ያሉ ቁጥር ሥፍር የሌላቸው ጆሮ ጠቢዎች በኢትዮጵያን ላይ የሚዘሩት ፍርሃት ቀላል አይደለም። ለምሳሌ ያህል አጠቃላይ አገራዊ ስምምነት የተደረሰ በሚመስል መልኩ፤ በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩ ግለሰቦች ድምጻቸውን የሹክሹክታ ያህል አሳንሰው ሲያወሩ ማየት ያልተለመደ አይደለም። በተለይ በመዲናችን አዲስ አበባ የራስ ትከሻን እየተጠራጠሩ ማውራት ወይም በታክሲ እንዲሁም በሻይ ቤቶች ቁጭ ብለው የሚወያዩ ሰዎች አፋቸውን ከልለው ማውራታቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። በዚህም አስፈሪ እና ዝግ በኾነ ምህዳር ምክንያት ዜጎች ዝምታን መርጠዋል። ዝምታውም ከቁጥጥራቸው በላይ የኾነውን ስለላ በተቃውሞ መግለጻቸውን ዋነኛ ማሳያ ነው። “ዝም ባለ አፍ ዝምብ አይገባም” መሠል አባባሎች አሁን የሚታየውን የፍርሃት ጥግ የሚገልጹ ናቸው። 

አጠቃላይ አፈናው ፈርጀ ብዙ ነው፤ መንግሥት ላይ ያላቸው ልዩነት በሰላ ብዕር የሚከትቡትን ጦማሮች እና ድረ ገፆች ያግዳል፣ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ የስለላ ሶፍትዌሮችን በመግዛት በአገር ውስጥም ኾነ ባህር ማዶ ያሉ ዜጎቹን ይሰልላል እንዲሁም ምስጠራን የሚያግዙ መመሪያዎችን ተጠቅማችኋልም ብሎ ጦማሪያንን ያስራል። በአሁኑ ጊዜ የሃሰት ስሞችን ወይም የብዕር ስሞችን መጠቀም ልክ በአደባባይ ሲያወሩ ኋላ እና ፊትን ገልመጥ እያሉ ወይም አፍን ከለል አድርጎ ማውራት ዓይነት በመስመር ላይ ግንኙነት የሚስተዋል ጠባይ ኾኗል። ብዙዎች ማንነታቸውን ለአደጋ የማያጋልጡ የሃሰት ስሞችን ካልተጠቀሙ በስተቀር የማህበራዊ ገጾች ተሳትፏቸው እጅግ ዝቅተኛ ነው። ፖለቲካ ነክ ጉዳዮች ላይ አስተያየት አይሰጡም፣ አያካፍሉም ወይም ማንበባቸውን የሚጠቁም ምልክት አያሳዩም። የመንግሥት ሥርዓት የለሽ ክስ እና እስራት (በርካታ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች እንዲሁም የማኅበራዊ ድረገጽ ተጠቃሚዎች ሃሳባቸውን ብቻ በመግለጻቸው በግፍ መታሰር እና መወንጀል) ለብዙሃን ፍርሃት ምክንያት ኾኗል።

ይሁንና ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ ችግሩ ውስብስብ ኾኖ ይታያል። የሃሰት ስሞችን ተጠቅሞም በአደባባይ ሃሳብን መግለጽ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች ዋስትና ላይኖረው ይችላል። ለምሳሌ ያህል በአሜሪካ አገር መቀመጫውን ያደረገው የኢትዮጵያዊው የተመሳሳይ ጾታ መብት አቀንቃኝ የፌስቡክ ገጽ ከተጠቃሚዎች በተላኩ በርካታ መልዕክቶች በሚል ሰበብ እንዲዘጋ ተደርጎ ነበር። ፌስቡክ የተላኩለት መልዕክቶች ጥላቻን መሠረት አድርገው የተፈበረኩ መኾናቸውን ተረድቶ ገጹን በመጨረሻ ለባለቤቱ ቢመልስም፤ አጋጥሚው ግን የስውር ስም ወይም ምስጢራዊነትን መጠቀም ብቻውን የመንግሥትን አፋኝነት ጥሶ ለማለፍ በቂ አለመኾኑን አሳይቷል።

ራስን ከስለላ የመከላከያ ብልሃቶች መመሪያ በአማርኛ እንደ መፍትሄ?

ይህንን የስለላ መከላከያ ብልሃቶች መመሪያ ለመተርጎም ሞያዊ እና ግለሰባዊ ምክንያቶች ነበሩኝ። በመጀመሪያ ደረጃ ውስብስብ እና ሕገ-ወጥ የኾነው የስልክ መጥለፍ ስለላ ተጠቂ ነኝ። በ2005 ዓ.ም ኢትዮጵያ ውስጥ በነበርኩበት ወቅት መንግሥት ስልኬን ጠልፏል። ይህንንም የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ባልደረቦቼን እና ወዳጆቼን ሕጋዊ ባልኾነ መንገድ ለመወንጀል ተጠቅሞበታል። እንዴት የስልክ አገልግሎት ሰጪው ኢትዮቴሌኮም ስልኮች እንዲጠለፉ ለመንግሥት ፍቃዱን ሰጠ ብለው ለሚጠይቁ የዋህ አንባቢዎች መልሱ ግልጽ ነው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ አገልግሎት ሰጪ ሲኾን ያለው ንብረትነቱም የመንግሥት ነው። በዚህም ምክንያት የማንኛውም ግለሰብ የስልክ ግንኑኘት መንግሥት በፈለገው ግዜ ሁሉ ይጠለፋል።  ይህ ወደ አማርኛ የተረጎምኩት የስለላ መከላከያ መመሪያ ችግሩን ሁሉ ይቀርፋል ብዬ ባልናገርም፤ የሚልዮኖችን ግላዊነት ለማስጠበቅ ግን አንዱ እርምጃ ነው የሚል ዕምነት አለኝ። በአንድ በስለላ በተከበበ ሥርዓት ውስጥ እንደመኖሬ መጠንም መመሪያውን በአገራችን ቋንቋ ማዘጋጀቱ የእኔም ኃላፊነት እንደኾነ አስባለሁ። ስለዚህም መመሪያውን ወደ አማርኛ መመለሱ በሕይወቱ የስለላን አስከፊነት የተገነዘበ ወይም የሥርዓቱ ሰለባ የኾነ ግለሰብ የሰጠው ምላሽ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ዘወትር በመንግሥት የስለላ መረብ ውስጥ ሌት ተቀን መከራቸው ለሚያዩ ዜጎች የሚደረግ አንዱ የድጋፍ ዘመቻ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል።

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በዘመነው ዓለም ጥቂት ዓመታትን እንደማስቆጠሬ እራሴን የኢትዮጵያ የዲጂታል ከባቢ “አንትሮፖሎጂስት” አድርጌ እቆጥረዋለሁ። ኢትዮጵያ ለሰዓታት አልፎም ለቀናት የኤሊክትሪክ ኃይል የሚቆረጥባት ስትሆን በርካቶች የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ኢንተርኔት ካፌዎችን የሚያጨናንቁባት አገር ናት። ኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጡ ሳይበግራቸው ለሰዓታት በኢንተርኔት ካፌ ውስጥ የሚገለገሉ በርካቶች ናቸው። አዲስ አበባ በነበርኩበት ወቅት በመብራት መቆራረጥ ምክንያት ሳይዘጉ የተተዉ የሌሎች ሰዎችን ፌስቡክ እና ኢሜል የመዝጋት ኃላፊነት አጋጣሚዎች ነበሩኝ። ብዙዎች ስለድረገጽ የደህንነት ጉዳዮች በቂ መረጃ እንደሌላቸው ተገንዝብያለሁ። ከአስተዋልኳቸው የተጠቃሚዎች ደካማ የድረገጽ አጠቃቀም ጠባይ የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው። የድር ማሰሻውን ድርብርብ በኾነው ማመስጠሪያ አለመጠቀም፣ ለሁሉም የመስመር ላይ ግንኙነት ተመሳሳይ ወይም ደካማ የኾኑ ማለፊያ ቃላትን መጠቀም፣ ደህንነቱ ያልጠረጋገጠ ድረ ገጽ መክፈት፣ ስምምነቶችን እና የደረገጽ ደንቦችን በወጉ ሳያስተውሉ መፈረም እንዲኹም ለሰርጎ ገቦች መረጃን አሳልፎ መስጠት እና የመሳሰሉት። እንደዚህ ዓይነት ስህተቶች ይህን የአማርኛ ትርጉም የበለጠ አስፈላጊ ያደርጉታል። በተጨማሪም ዊኪ ሊኪስ በቅርቡ ኢትዮጵያ ከሃኪንክ ቲም ውድ የኾነ የስለላ ሶፍትዌር መግዛቱን እነደዘገበው ሁሉ መንግሥት ዜጎቹን ለመሰለል ብዙ ገንዘብ ያወጣል እና እንዲህ ዓይነቱ መመሪያ መዘጋጀቱ ጠቀሜታው የጎላ ነው። ይህንን መመሪያ በአማርኛ በማተምም፣ በሚያካሂዳቸው መጠነ ሠፊ የስለላ ወንጀል የኢትዮጵያ መንግሥትን ለፍርድ ለማቅረብ ኢ.ኤፍ.ኤፍ የሚያደርገውን ጥረት ያጎላዋል።

ስለ ትርጉም ሥራው

እራስን ከስለላ የመከላከያ ብልሃቶች መመሪያ ውስብስብ ጉዳይ ነው። ይኹንና መመሪያውን በጥልቀት በማንበብ እና ተግባራዊ ሙከራዎችን በማድረግ የአማርኛው መመሪያ ይበልጥ ተነባቢ እና ቀላል እንዲኾን ጥረት አድርጊያለሁ። ማንኛውም አንባቢ እንደሚረዳው አማርኛችን በቴክኖሎጂ ቃላት የበለጸገ አይደለም። ለምሳሌ ያህል በኢንክሪፕሽን እና በክሪፕቶግራፊ ያለውን ልዩነት በአማርኛ ለማስቀመጥ ይቸግራል። እንዲህ ዓይነት ጉዳይ በሚያጋጥም ወቅትም በአውደ ንባቡ አንባቢ እንዲረዳው ተጨማሪ ማብራሪያ እንድጽፍ አስገድዶኛል። እንዲሁም እንደ ኦፕን ሶርስ፣ ዳታ፣ ሊንክ፣ ዳታ ቢዝ፣ እና ዶሜይን ኔም የመሳሰሉት የቴክኖሎጂ ቃላት ሲያጋጥሙኝ የአማርኛ-ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላት እንዲሁም መደበኛውን የአማርኛ-እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት በመጠቀም ፍቻቸውን አስቀምጫለሁ። በተጨማሪም “ጌይ” የሚለውን ያለ ምንም ቅጥያ ለማስተዋወቅ ስለፈለግሁ “ሓዋረ ብእሲ” የሚለውን ፍቺ ከዎልፍ ሌስላው ግዕዝ-እንግሊዝኛ መዝገባ ቃላት ተጠቅሚያለሁ። ይህም በኢትዮጵያዊው ጦማር ላይ ተጠቅሶ ይገኛል።

ማጠቃለያ

ግለሰቦች የመስመር ግንኙነታቸውን ደህንነት እንዲጠብቁ ማስተማር አንዱ የግላዊነት መብት ተከራካሪነት ተግባር ነው። መንግሥት እና የሕግ አስፈጻሚው አካል እንደ ሕግ ስለላን ወስደው ዜጎችን በቁጥጥር ውስጥ በሚያስገቡ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ደግሞ አስፈላጊነቱ የጎላ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ስለላ የሚያካሂደው ለዜጎቹ ደህንነት አስቦ እንደኾነ በመከራከል ለማሳመን ይሞክራል። እውነታው ይህ እንዳልኾነ ጸሐይ የሞቀው ጉዳይ ቢኾንም። ይህ የአማርኛ መመሪያ ዜጎች ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲቆዩ ግላዊነትን መመሪያቸው እንዲያደርጉ ይመክራል፤ ያስተምራልም።

Share this:   ||  Join EFF


Source: https://www.eff.org/node/88081


Before It’s News® is a community of individuals who report on what’s going on around them, from all around the world.

Anyone can join.
Anyone can contribute.
Anyone can become informed about their world.

"United We Stand" Click Here To Create Your Personal Citizen Journalist Account Today, Be Sure To Invite Your Friends.

Please Help Support BeforeitsNews by trying our Natural Health Products below!


Order by Phone at 888-809-8385 or online at https://mitocopper.com M - F 9am to 5pm EST

Order by Phone at 866-388-7003 or online at https://www.herbanomic.com M - F 9am to 5pm EST

Order by Phone at 866-388-7003 or online at https://www.herbanomics.com M - F 9am to 5pm EST


Humic & Fulvic Trace Minerals Complex - Nature's most important supplement! Vivid Dreams again!

HNEX HydroNano EXtracellular Water - Improve immune system health and reduce inflammation.

Ultimate Clinical Potency Curcumin - Natural pain relief, reduce inflammation and so much more.

MitoCopper - Bioavailable Copper destroys pathogens and gives you more energy. (See Blood Video)

Oxy Powder - Natural Colon Cleanser!  Cleans out toxic buildup with oxygen!

Nascent Iodine - Promotes detoxification, mental focus and thyroid health.

Smart Meter Cover -  Reduces Smart Meter radiation by 96%! (See Video).

Report abuse

    Comments

    Your Comments
    Question   Razz  Sad   Evil  Exclaim  Smile  Redface  Biggrin  Surprised  Eek   Confused   Cool  LOL   Mad   Twisted  Rolleyes   Wink  Idea  Arrow  Neutral  Cry   Mr. Green

    MOST RECENT
    Load more ...

    SignUp

    Login

    Newsletter

    Email this story
    Email this story

    If you really want to ban this commenter, please write down the reason:

    If you really want to disable all recommended stories, click on OK button. After that, you will be redirect to your options page.